News and Events |
የቀን እና የማታን ሰልጣኞችን ይመለታል |
![]() |
Date Posted: 2025-03-13 09:27:53 |
የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምርጥ ተሞክሮ በኮሌጁ ዲን በአቶ ባሻዬ በየነ ቀረበ |
የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አመራሮች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ የካቲት 9/2017ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ ላይ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምርጥ ተሞክሮ በኮሌጁ ዲን በአቶ ባሻዬ በየነ ቀርቧል።በቀረበውም ተሞክሮ ውይይት ተደርጓል |
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |
Date Posted: 2025-02-18 00:57:14 |
የደብረ ብርሃን ፖሊ ትክኒክ ኮሌጅ የ ISO ትግበራላይ ነዉ |
ISO 9001:2015 ማለት ምን ማለት ነው? ISO 9001:2015 የሚለው የአለም አቀፍ ደረጃ ለጥራት አስተዳደር ስርዓት (Quality Management System - QMS) የሚያቀርብ መመሪያ ነው። ይህ ደረጃ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን በተጠበቀ መልኩ ለደንበኞች እንዲያቀርቡ የሚያስችል አግባብነት ያለው ስርዓት እንዲመሰርቱ ይረዳቸዋል። የISO 9001:2015 ደረጃ በማንኛውም የኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰራ ድርጅት ሊተገበር ይችላል። ISO 9001:2015 መተግበር ለምን ይጠቅማል? ISO 9001:2015 መተግበር ለድርጅቶች ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል። ከነዚህም መካከል ዋነኛዎቹ የሚከተሉት ናቸው። የጥራት ማሻሻያ ISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓትን በመተግበር ድርጅቶች ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን በተጠበቀ መልኩ ለደንበኞች እንዲያቀርቡ ይረዳቸዋል። ይህም የምርት ጥራትን ያሻሽላል እና የደንበኞችን እርካታ ያሳድጋል። የደንበኞች እርካታ ማሳደግ ይህ ደረጃ የደንበኞችን ፍላጎቶች እና የሚጠበቁትን ውጤት ለመረዳት እና ለማሟላት የሚያስችል ስርዓት ያቀርባል። ይህም የደንበኞችን እርካታ ያሳድጋል እና የድርጅቱን ምርት እና አገልግሎት በገበያ ውስጥ የማረጋገጥ አቅም ይጨምራል። የውስጥ ሂደቶች ማሻሻያ ISO 9001:2015 የውስጥ ሂደቶችን ለማሻሻል እና ለማመቻቸት የሚያስችል መርሆዎችን ያቀርባል። ይህም የድርጅቱን ውጤታማነት ያሳድጋል እና ወጪዎችን ይቀንሳል። የደንበኞች እምነት ማሳደግ ISO 9001:2015 የሚለው የአለም አቀፍ ደረጃ የተረጋገጠ የጥራት አስተዳደር ስርዓት እንዳለው የሚያሳይ ምልክት ነው። ይህም የደንበኞችን እምነት ያሳድጋል እና የድርጅቱን ተወዳዳሪነት በገበያ ውስጥ ያሻሽላል። የአለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ISO 9001:2015 የአለም አቀፍ ደረጃ በመሆኑ ድርጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ላይ እንዲወዳደሩ ያስችላቸዋል። ይህም በተለይም ለምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን ወደ ውጭ ለመላክ የሚፈልጉ ድርጅቶች በጣም ጠቃሚ ነው። የህግ እና ደንብ መሟላት ISO 9001:2015 የሚያስፈልጉትን ህጎች እና ደንቦች ለመሟላት የሚያስችል ስርዓት ያቀርባል። ይህም ድርጅቶች ከህግ ጋር የሚጋጩ ችግሮችን ለማስወገድ ይረዳቸዋል። የሰራተኞች ተሳትፎ ማሳደግ ISO 9001:2015 የሰራተኞችን ተሳትፎ እና ተጠያቂነት ለማሳደግ የሚያስችል ስርዓት ያቀርባል። ይህም የሰራተኞችን ምክንያታዊነት እና የሥራ እርካታ ያሳድጋል። ማጠቃለያ ISO 9001:2015 መተግበር ለድርጅቶች በጥራት አስተዳደር፣ የደንበኞች እርካታ፣ የውስጥ ሂደቶች ማሻሻያ እና የአለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ላይ ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል። ይህ ደረጃ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ራሳቸውን ለማሻሻል እና በገበያ ውስጥ የተሻለ ቦታ ለማግኘት ይረዳቸዋል። |
![]() |
Date Posted: 2025-01-29 02:19:26 |
የደብረ ብርሃን ፖሊ ትክኒክ ኮሌጅ የ ISO ሳምንት በማክበር ላይ ይገኛል |
![]() |
Date Posted: 2025-01-29 02:16:01 |
የአማራ ክልል ስራና ስልጠና ቢሮ የደብረብርሃን ከተማ እና የሰሜን ሸዋ የፖሊ ቴክኒክ እና የኮሌጆች የ4 ወራት አፈፃጸም ግምገማ እያካሄደ ነው |
«በበጀት ዓመቱ ለ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው» - አማረ አለሙ ደብረብርሃን ፡ ኅዳር 4/2017ዓ.ም የአማራ ክልል ስራና ስልጠና ቢሮ የደብረብርሃን ከተማ እና የሰሜን ሸዋ የፖሊ ቴክኒክ እና የኮሌጆች የ4 ወራት አፈፃጸም ግምገማ እያካሄደ ነው የአማራ ክልል ስራና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አማረ አለሙ ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንደተናገሩት የመድረኩ ዓላማ የሩብ ዓመቱን አፈፃጸም በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል። ኮሌጆች በተሰጣቸው የ100 ቀናት ዕቅድ መሠረት አፈፃጸሙን በመገምገም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና እጥረቶችን ለማስተካከል የውይይት መድረኩ መመቻቸቱን አንስተዋል። በተለይም ከመደበኛ ስልጠና በዘለለ ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራ ስልጠና በመስጠት ዜጎች ሰርተው ራሳቸውን እንዲለውጡ ኮሌጆች እና የዘርፉ ተዋናዮች ብዙ መስራት እንዳለባቸው አመልክተዋል። በመንግስት ድጋፍ ተደርጎላቸው ዘላቂ እና ወደ መካከለኛ ባለሃብት የሚሸጋገሩ ወጣቶችንና ኢንተርፕራይዞችን ለማፍራት አንድ የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ከዚህ በተጨማሪ በዲጅታላይዜሽን ዘርፍ ኮሌጆች የማስፋፋት ስራዎችን እንዴት እየተገበሩ እንደሆነና በሌሎችም ተግባራት ላይ ውይይቱ የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚሁ መሠረት በ2017 ዓ.ም 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎቸ የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በተያያዘም በመደበኛ ትምህርትና ስልጠና 198ሺ ፣ በኢንተርፕራይዝ ስልጠና 958ሺ፣ በቴክኒካል ስልጠና 456ሺ ወጣቶችን ለማሰልጠን መታቀዱን አመልክተዋል። የደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ባሻየ በየነ የኮሌጃቸውን ዕቅድ አፈፃጸም አቅርበዋል። በግምገማ መድረኩ የደብረ ብርሃን ከተማ እና የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች፣ የስራና ስልጠና የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል። |
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |
Date Posted: 2024-11-15 05:06:44 |
የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ የ2017ዓ.ም በጀት አመት የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የሱፐርቪዥን ቡድን በደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሠረት ግምገማ እያደረጉ ይገኛል። |
የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ የ2017ዓ.ም በጀት አመት የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የሱፐርቪዥን ቡድን በደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሠረት ግምገማ እያደረጉ ይገኛል። |
![]() ![]() ![]() ![]() |
Date Posted: 2024-11-12 21:14:11 |
ኮሌጁ በቀጣይ 3 እና 4 ወራት ውስጥ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን የISO ሰርተፍኬት ለማግኘት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ |
ደብረብርሃን፣ጥቅምት 22/2017(ደብኮ):- የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቀጣይ 3 እና 4 ወራት ውስጥ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን የISO 9001/2015 ሰርተፍኬት ለማግኘት ለመምህራን እና ሠራተኞች ስልጠና እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል። የኮሌጁ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ እንደገለጹት ኮሌጃቸው አዳዲስ እሳቤዎችን መነሻ በማድረግ ለኢንተርፕራይዞች፣ ለደብረብርሃንና ለሰሜን ሸዋ አካባቢዎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አንስተዋል። ለተሽከርካሪዎች የቦሎ ምርመራ ፣ለሾፌሮች ስልጠና በመስጠት በአንድ በኩል ለህብረተሰቡ ተስማሚ አገልግሎት እንዲሰጡ፣ በሌላ በኩል ደረጃቸውን እንዲያሳድጉ ተቋማቸው እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። በተለይም በክልሉ ከፍተኛ ሰልጣኝ ተቀብሎ በጥራት በማሰልጠን ተወዳዳሪነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስታውቀዋል። የኮሌጁን ተወዳዳሪነት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግ በISO 9001/2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ዙሪያ 3 መቶ ለሚሆኑ መምህራን እና ሠራተኞች ስልጠና እየሰጡ መሆኑን አቶ ባሻዬ አመልክተዋል። ስልጠናው የዓለም አቀፍ ደረጃ መስፈርት ያሟላ እንዲሆን በISO የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት እና በISO ኦዲቲንግ ዙሪያ ለ5 አሰልጣኝ መምህራን በኢትዮጵያ ጥራትና ደረጃዎች ባለስልጣን ስልጠና መውሰዳቸውን አስረድተዋል። ኮሌጃቸው ከስልጠና በኃላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትግበራ እንደሚገባና በቀጣይ 3 እና 4 ወራት ውስጥ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን የISO ሰርተፍኬት ለማግኘት እየሰራ መሆኑን አስታወቀዋል። በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተቀባይነት ያላቸው ሰልጣኞችን ለማፍራት የኮሌጁ የስራ ኃላፊዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች ከፍተኛ መነሳሳት ማሳየታቸውን እና መግባባት ላይ መድረሳቸውን ዲኑ አብራርተዋል። የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጥራት ማረጋገጥ ኃላፊ ኢንስትራክተር ተስፋዬ አያሌው በበኩላቸው እንደገለጹት ISO ብዙ ጊዜ ለትልልቅ ኩባንያ እና ለምርት ተቋም ብቻ ሳይሆን ከትንሽ እስከ ትልቅ ተቋም የሚያገለግል የስራ አመራር ስርዓት የሚዘረጋ መሆኑን አመልክተዋል። ተቋማቸው ISO 9001/2015 ወይም የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ለመተግበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል። ISO ስራ በቀላሉ እንዲሰራ የሚያደርግ ፣ምርታማነትን የሚጨምር፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የደንበኛ እርካታን የሚያሳድግ፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚሁ መሠረት ተቋማቸው ከዚህ በፊት የሚታወቅበትን አሻሽሎ ISOን በመተግበር የሰልጣኞችን ፣የኢንተርፕራይዞችን፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ እና የመንግስትን እርካታ በማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚሰራ አመልክተዋል። |
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |
Date Posted: 2024-11-04 16:48:29 |
የ 2017 ዓ.ም የአዲስ ተማሪዎች ቅበላን ይመለከታል… |
![]() |
Date Posted: 2024-10-25 00:29:35 |
ለ2017 አዲስ ለስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ የደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አደረሳችሁ እያለ አዲስ ሰልጣኝ ቅበላ የምናደርግባቸዉ ሙያዎች የአካባቢዉን የመልማት ፀጋ ተለይቶ በተፈቀዱልን 5 ዘርፎች ብቻ (Distinctive area of competency /DAC) መሰረት 12ኛ ክፍል አጠናቃችሁ በተለያየ የዉጤት ይዛችሁ ስልጠና ፈላጊዎች ከ ደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 የምናሰለጥን መሆኑን አዉቃችሁ ስልጠና ፈላጊዎች እንደየ ዉጤታችሁ ለየደረጃችሁ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ እስኪሆን ድረስ ደብረንርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የምንሰጣችዉን የስልጠና አይነቶች እና ደረጃ እንደሚከተለዉ እያሳወቅን የምዝገባ ቀኑን እና መስፈርቱን በቅርብ ስለምናሳዉቃችሁ ቅድመ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁን በአክብሮት እናሳዉቃለን ፡፡ ስልጠና የምንሰጥባቸዉ ሙያዎች ደረጃዎችን ከስር ይመልከቱ |
![]() |
Date Posted: 2024-09-24 12:45:19 |
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስራና ስልጠና ቢሮ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባመጣዉ አመርቂ ዉጤት የእዉቅና የምስክር ወረቀት አበረከተ |
የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የእዉቅና የምስክር ወረቀት |
![]() ![]() |
Date Posted: 2024-08-14 18:44:58 |
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስራና ስልጠና ቢሮ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባመጣዉ አመርቂ ዉጤት የእዉቅና የምስክር ወረቀት አበረከተ |
የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ የእዉቅና የምስክር ወረቀት ሲቀበሉ |
![]() |
Date Posted: 2024-08-14 18:43:24 |
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስራና ስልጠና ቢሮ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባመጣዉ አመርቂ ዉጤት የእዉቅና የምስክር ወረቀት አበረከተ |
እንኳን ደስ አላችሁ !!! የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአብክመ የስራና ስልጠና ቢሮ ባዘጋጀዉ በ2016 በጀት ዓ.ም በአደረገዉ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በ 1ኛ ደረጃ በመዉጣት ይህ እዉቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰቶታል እንዲሁም የላብቶብ ተሸላሚ መሆን ችለናል የኮሌጁ መምህራን እና ሰራተኞች በሙሉ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን ፡፡ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ነሐሴ 8/2016 |
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |
Date Posted: 2024-08-14 18:32:22 |
Guest of honor Ato Bedilu mayor of Debre Birhan Regio Politian City Administration place message D/B Polytechnic Graduate |
Guest of honor Ato Bedilu mayor of Debre Birhan Regio Politian City Administration place message D/B Polytechnic Graduate |
![]() ![]() |
Date Posted: 2024-07-15 18:59:24 |
DBPTC Leaders at Graduation Hall |
DBPTC Leaders at Graduation Hall |
![]() |
Date Posted: 2024-07-15 18:51:50 |
2016E.C Graduation |
2016E.C Graduation |
![]() |
Date Posted: 2024-07-15 18:46:58 |
High Score Achiever |
High Point Achiever |
![]() |
Date Posted: 2024-07-15 18:29:09 |
Debre Polytechnic Dean |
Debre Polytechnic Dean Ato Bashaye Beyene place his statement during Graduation |
![]() |
Date Posted: 2024-07-15 17:37:54 |
Graduation |
![]() |
Date Posted: 2024-07-15 17:34:31 |
Graduation |
2016E.C Graduation |
![]() |
Date Posted: 2024-07-15 17:29:52 |
Our Great Achievement |
Debre Birhan Polytechnic College got reward due to high achievement compared across the country. |
![]() |
Date Posted: 2024-07-15 16:58:35 |
የአይቲ ሰልጣኞች ተቋማዊ ምዘና ወሰዱ |
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ት/ም ክፍል ሰልጣኞች ተቋማዊ ምዘና ወሰዱ |
Date Posted: 2024-07-13 19:19:29 |
በተለያዩ ሙያ የሰልጠኑ ሰልጣኞች ተቋማዊ ምዘና ወሰዱ |
በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ት/ም ክፍል ያሉ ሰልጣኞች ተቋማዊ ምዘና ወሰዱ |
Date Posted: 2024-07-13 19:17:23 |
የኮሌጃችን ስኬት |
በፌደራል ደረጃ በተካሄደው አጠቃላይ የቴክንክና ሙያ ኮሌጆች ውድድር #የደብረብርሃን_ፖሊቴክንክ_ኮሌጅ አንደኛ ደረጃ ወጥቷል። የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ሦስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች እውቅና ተሰጣቸው በክህሎት ልማት ዘርፉ ተግባራዊ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከማሰልጠን በላይ ተልዕኮ ወስደው ወደ ተግባር ገብተዋል፡፡ በሪፎርሙ ተቋማቱ ኢንተርኘሪነራል እሳቤን ተላብሰው ሥራ ፈላጊ ዜጎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከመደበኛው ሥልጠና ጎን ለጎን አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ኢንተርፕራዞችን በማደራጀት፣ ወደ ሥራ ለገቡ ኢንተርፕራይዞችን ቀጣይነት ያለው ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የማሰልጠኛ ተቋም ብቻ ሳይሆን ለሥራ ዕድል ፈጠራው የዕድል በሮችም ጭምር ሆነው የሚያገለግሉበት አቅጣጫ ተቀምጦ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረትም የተቋማትን የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም መነሻ በማድረግ ሦስት ምርጥ ተቋማት በመጀመሪያው የአፍሪካ የሥራ ጉባኤ ላይ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም መሰረት የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አንደኛ፣ አዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሁለተኛ እንዲሁም የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሦስተኛ በመሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ በመሆናቸው እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ |
![]() |
Date Posted: 2024-07-13 19:02:24 |
የትራንስፖርት ቴክኒሽያን ብቃት ማረጋገጫ የአሽከርካሪዎች የመግቢያ ፈተና |
ከሁለተ አስርተ አመታተ በላይ ህብረተሰባችንን ቅንነት እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞቻችን ብዙዎችን ባለሙያ ማድረጋችን ይታወቃል ፡፡ አሁን ደግሞ ከዚህ በፊት ቃል በገባነዉ መሰረት የትራንስፖርት ቴክኒሽያን ብቃት ማረጋገጫ ተቐማችን በዚህ መልኩ በቀን 09/08/2016 አሽከርካሪዎችን የመግቢያ ፈተና በመስጠት ስልጠና በይፋ መጀመራችንን እየገልፅን ከዚህ በኃላ ማንኛዉም አሽከርካሪ ስልጠናዉን በመዉሰድ የትራንስፖርት ባለቤት መሆን እንደምትችሉ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን ፡፡ የደ/ብርሀን ፖሊ/ቴ/ኮሌጅ የተሽከርካሪዎች ቴክኒሽያን ብቃት ማረጋገጫ ተቐም !!! |
![]() |
Date Posted: 2024-07-13 18:20:58 |
የተሽከርካሪ ምርምራ መስጠት ተጀመረ |
ኮሊጃችን የተሽከርካሪ ምርምራ መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርገ |
![]() |
Date Posted: 2024-07-13 15:42:54 |
የትራንስፖርት ቴክንሽያን ብቃት ማረጋገጫ(አፕሩቫል) |
ኮሌጃችን የትራንስፖርት ቴክንሽያን ብቃት ማረጋገጫ(አፕሩቫል) ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቀቀ |
![]() |
Date Posted: 2024-07-13 15:36:17 |
Sustainable Employment through Entrepreneurship & Enterprise Development (Seed) Project Training |
የደብረ ብርሀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ Sustainable Employment through Entrepreneurship & Enterprise Development (Seed) Project ላይ ለደብረ ብርሀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች፣ ዲፖርትመንት ተጠሪዎች፣ አጠቃላይ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም ከደ/ብርሀን ሪጅዮ ፖሊታን ስራና ስልጠና መምሪያ የስራ እድል ፈጠራ ቡድን መሪና የስልጠና ቡድን መሪዎች ባሉበት በ08/06/2016ዓ.ም ለአንድ ቀን በአቶ ባሻዬ በየነ በደ/ብርሀን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን በሆኑት ስልጠና የተሠጠ ሲሆን የኮሌጁ ማህበረሰብም ፕሮጀክቱ የሚጠበቅበትን ለማበርከት ዝግጁ መሆንን አረጋግጠዋል |
![]() |
Date Posted: 2024-07-13 15:26:10 |