በክልል ሲካሄድ የሰነበተው የቴክኖሎጂ ክህሎት፤ የተግባር ጥናትና ምርምር ውድድር ላይ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአጠቃላይ ውድድር 1ኛ ደረጃ በመሆን አሁንም ውድድሩን ጨርሳል። እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን !!! እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን !!! "'ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች '' በሚል መሪ መልዕክት የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ አዘጋጅነት ከሚያዚያ 18_23/2017ዓ.ም ድረስ በአሠልጣኞች ፤ሠልጣኞች፤ኢንተርፕራይዞች እና ስራ ፈጣሪ ወጣቶች መካከል በኮምቦልቻ ከተማ ለ9ኛ ጊዜ በተካሄደው ክልላዊ የቴክኖሎጅ፣ የክህሎት፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ፣ ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግር እዉቅናና የንግድ ትርዒት ኤግዚቪሽን ውድድር ላይ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 57 ሜዳሊያዎችን በመሠብሠብ በአጠቃላይ ውጤት 1ኛ ደረጃ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። ውድድሩ የእርስ በእርስ የእውቀት የክህሎትና የአሰራር ልምዶችን ያካፈለ ከመሆኑ ባሻገር ችግሮችን በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በክህሎት ስራዎች ለመፍታት ወሳኝ መሆኑን ያሳየ ውድድር ተካሂዳል።ውድድሩም በየደረጃው ማለትም በኮሌጅ፣ ደረጃ ፣ በክላስተር ደረጀ ፣ በክልል አቀፍ ደረጃ ሲሆን ይሄን ብርቱና ጠንካራ ውድድር በማሸነፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአሸናፊዎች አሸነፉ በአ.አበባ ከሚያዚያ 27 - ግንቦት 2/ 2017 ይካሄዳል። በውድድሩ በተገኘው ውጤት የተሳተፋችሁ ሁሉ ምስጋና እያቀረብን በድጋሚ እንኳን ደስ አለን:: |