እንኳን ደስ አላችሁ ደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ISO 9001-2015 (QMS) ተግባራዊ በማድረጉ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ተሰጠው። ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን ሊያገኝ ችሏል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለኮሌጁ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ ሰርቲፊኬቱን አስረክበዋል፡፡ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። እንኳን ደስ አለን ! እንኳን ደስ አላችሁ በዚህም ለኮሌጃችን አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ለኮሌጃችን ኳሊቲ ማኔጀርና ኢንተርናል ኳሊቲ ኦዲተር አባላት ይህን ስኬት ለማግኘት በምናደርገው ጥረት ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ላደረጋችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። |