News and Events | Show More |
የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮልጅ በ7 የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 መቶ 33 ተማሪዎች እያስመሰቀ ነው። |
ደብረ ብርሃን፦ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮልጅ ለ27ኛ ዙር በ7 የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 መቶ 33 ተማሪዎች በአፄ ምኒልክ አዳራሽ እያስመሰቀ ይገኛል። ከሰልጣኞች መካከል 2 መቶ 80 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 3 መቶ 53ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውንና ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 5 የሰለጠኑ መሆናቸውን የኮሌጁ ዋና ዲን የኮሌጁ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ ገልጸዋል። የኮሌጁ ኃላፊ በማንፋከቸሪንግ ፣ በኤሌክትሪክሲቲ ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ በጋርመንት ፣ በአውቶሞቲቭ ፣ በሆቴልና ቱሪዝም ፣ በሰርቬይንግ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች በዛሬ እለት እያስመረቀ ነው ብለዋል አቶ ባሻዬ እንዳሉት ኮሌጁ ከተመሠረተበት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ በመደበኛው የትምህርት መርሐ-ግብር ብቻ ከ28 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን አስመርቆ ወደ ሥራ ማሠመራቱን ገልጸዋል። ኮሌጁ በዚህ ዓመት ብቻ ለ27 ሺህ 7 መቶ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ጨምሮ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች አጫጭር ሥልጠና መስጠቱን አቶ ባሻዬ ተናግረዋል። በዛሬው እለት የእናንተ አንዱናየመጀመሪያው የሕይወታችሁ ምዕራፍ እንደመሆኑ ከሰለጠናችሁበት ሙያ በተጨማሪ አዳዲስ እውቀትና የሥራ ላይ ክህሎት እየጨመራችሁበት ሊያሠራችሁ በሚችል ቦታና ጊዜ እንድትጠቀሙበት እየተማመንኩ ችግሮችን ሁሉ በመጋፈጥ ተወዳዳሪ ሆናችሁ ያስተማራችሁን ማኅበረሰብ በሙያችሁ በፍጹም ቅንነት ፣ ታማኝነት እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ ብለዋል። ጥሪ የተደረገላችሁም እንግዶች የተመራቂ ቤተሰቦች ፣ የሁላችሁም ፍሬዎች የሆኑትን የዛሬ ምሩቃንን በማስመረቅ እዚህ በመገኘታችሁ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ሲሉ ተናግረዋል። የተመረቁ ሰልጣኞችን ከነገ ጀምሮ ተደራጅተው በተለያዩ ድርጅቶች ይሁን በግላቸው እንዲሰማሩ ከጎናቸው በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉላቸው እየጠየቅሁ ተመራቂዎችም መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ብለዋል። |
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |
Date Posted: 2025-07-13 05:05:48 |