Loading...

News and Events

ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ ዘርፎች ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና በማብቃት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው

📅 2025-10-11 08:46:08(23 days ago)

ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ ዘርፎች ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና በማብቃት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው። በተያዘው በጀት ዓመትም ከ19ሺህ 2መቶ በላይ ወጣቶች ገበያ ተኮር በሆኑ አጫጭር ስልጠናዎችና ቴክኒካል ስልጠና ወደ ስራ ለማስገባት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን በማንሳት ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ ጋር በመተባበር ለአንድ ወር በቧንቧ መስመር ዝርጋታና በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የሰለጠኑ 50 ሰልጣኞች ዛሬ በደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከአምሪፍ ኸልዝ አፍሪካ ጋር ውል ገብቶ ወጣቶቹን ያሰለጠነው የደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ በበኩላቸው ሰልጣኞች በተመረጡ የሙያ ዘርፎች ተገቢውን ተግባር ተኮር ስልጠና ወስደው 99ከመቶ የሚሆኑትም የሲኦሲ ምዘነውን በብቃት አጠናቀው የተመረቁ መሆናቸውን ገልፀዋል። የደብረብርሃን ከተማ ስራና ስልጠና መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ አይናለም ከፈለኝ እንዳሉት ስራ አጥ ዜጎችን በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች የቴክኒካል እና የአጫጭር ስልጠናዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት ከመንግስት አቅም ባለፈ የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው ብለዋል። የወሰድነው ስልጠና ተግባር ተኮር በመሆኑና ለስራ መነሻ የሚሆን ግብዓትም ከአምሪፍ በማግኘታችን በራስ አቅም ወደ ስራ ገብተን ከራሳችን ባለፈ ለሌሎችም የስራ እድል ለመፍጠር እንሰራለን ያሉት ደግሞ ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች ናቸው። (የፖ/ሊ / ኮ/ ህዝብ ግንኑነት)

Notice image for  ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ ዘርፎች ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና በማብቃት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው

የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ 2018 ዓ. ም የነባር መደበኛ ሰልጣኞችን የምዝገባ ቀን እና የስልጠና ቀን ይመለከታል;

📅 2025-09-24 05:12:43

Notice image for  የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ 2018 ዓ. ም የነባር መደበኛ ሰልጣኞችን የምዝገባ ቀን እና የስልጠና ቀን ይመለከታል;

የ 2017 ተመራቂ ተማሪዎችን ይመለከታል

📅 2025-08-12 11:04:07

Notice image for  የ 2017 ተመራቂ ተማሪዎችን ይመለከታል

አሻራ ምዝገባ ለምትፍልጉ

📅 2025-08-07 03:26:30

Notice image for  አሻራ ምዝገባ ለምትፍልጉ

የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮልጅ በ7 የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 መቶ 33 ተማሪዎች እያስመሰቀ ነው።

📅 2025-07-13 05:05:48

ደብረ ብርሃን፦ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮልጅ ለ27ኛ ዙር በ7 የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 መቶ 33 ተማሪዎች በአፄ ምኒልክ አዳራሽ እያስመሰቀ ይገኛል። ከሰልጣኞች መካከል 2 መቶ 80 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 3 መቶ 53ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውንና ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 5 የሰለጠኑ መሆናቸውን የኮሌጁ ዋና ዲን የኮሌጁ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ ገልጸዋል። የኮሌጁ ኃላፊ በማንፋከቸሪንግ ፣ በኤሌክትሪክሲቲ ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ በጋርመንት ፣ በአውቶሞቲቭ ፣ በሆቴልና ቱሪዝም ፣ በሰርቬይንግ ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች በዛሬ እለት እያስመረቀ ነው ብለዋል አቶ ባሻዬ እንዳሉት ኮሌጁ ከተመሠረተበት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ በመደበኛው የትምህርት መርሐ-ግብር ብቻ ከ28 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን አስመርቆ ወደ ሥራ ማሠመራቱን ገልጸዋል። ኮሌጁ በዚህ ዓመት ብቻ ለ27 ሺህ 7 መቶ ዜጎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ጨምሮ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች አጫጭር ሥልጠና መስጠቱን አቶ ባሻዬ ተናግረዋል። በዛሬው እለት የእናንተ አንዱናየመጀመሪያው የሕይወታችሁ ምዕራፍ እንደመሆኑ ከሰለጠናችሁበት ሙያ በተጨማሪ አዳዲስ እውቀትና የሥራ ላይ ክህሎት እየጨመራችሁበት ሊያሠራችሁ በሚችል ቦታና ጊዜ እንድትጠቀሙበት እየተማመንኩ ችግሮችን ሁሉ በመጋፈጥ ተወዳዳሪ ሆናችሁ ያስተማራችሁን ማኅበረሰብ በሙያችሁ በፍጹም ቅንነት ፣ ታማኝነት እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ ብለዋል። ጥሪ የተደረገላችሁም እንግዶች የተመራቂ ቤተሰቦች ፣ የሁላችሁም ፍሬዎች የሆኑትን የዛሬ ምሩቃንን በማስመረቅ እዚህ በመገኘታችሁ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ሲሉ ተናግረዋል። የተመረቁ ሰልጣኞችን ከነገ ጀምሮ ተደራጅተው በተለያዩ ድርጅቶች ይሁን በግላቸው እንዲሰማሩ ከጎናቸው በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉላቸው እየጠየቅሁ ተመራቂዎችም መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ብለዋል።

Notice image for  የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮልጅ በ7 የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6 መቶ 33 ተማሪዎች እያስመሰቀ ነው።

View All News
25928 views