Loading...

News and Events

ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ ዘርፎች ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና በማብቃት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው

📅 2025-10-11 08:46:08

ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ ዘርፎች ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና በማብቃት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው። በተያዘው በጀት ዓመትም ከ19ሺህ 2መቶ በላይ ወጣቶች ገበያ ተኮር በሆኑ አጫጭር ስልጠናዎችና ቴክኒካል ስልጠና ወደ ስራ ለማስገባት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን በማንሳት ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ ጋር በመተባበር ለአንድ ወር በቧንቧ መስመር ዝርጋታና በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የሰለጠኑ 50 ሰልጣኞች ዛሬ በደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከአምሪፍ ኸልዝ አፍሪካ ጋር ውል ገብቶ ወጣቶቹን ያሰለጠነው የደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ በበኩላቸው ሰልጣኞች በተመረጡ የሙያ ዘርፎች ተገቢውን ተግባር ተኮር ስልጠና ወስደው 99ከመቶ የሚሆኑትም የሲኦሲ ምዘነውን በብቃት አጠናቀው የተመረቁ መሆናቸውን ገልፀዋል። የደብረብርሃን ከተማ ስራና ስልጠና መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ አይናለም ከፈለኝ እንዳሉት ስራ አጥ ዜጎችን በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች የቴክኒካል እና የአጫጭር ስልጠናዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ ለማስገባት ከመንግስት አቅም ባለፈ የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነው ብለዋል። የወሰድነው ስልጠና ተግባር ተኮር በመሆኑና ለስራ መነሻ የሚሆን ግብዓትም ከአምሪፍ በማግኘታችን በራስ አቅም ወደ ስራ ገብተን ከራሳችን ባለፈ ለሌሎችም የስራ እድል ለመፍጠር እንሰራለን ያሉት ደግሞ ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች ናቸው። (የፖ/ሊ / ኮ/ ህዝብ ግንኑነት)

Notice image for  ገበያ ተኮር በሆኑ የስራ ዘርፎች ወጣቶችን በአጫጭር ስልጠና በማብቃት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ ነው

View All News
26616 views