📅 2025-11-13 11:36:40(23 days ago)
የውይይቱ ዓላማ ኢንዱስትሪዎች ከቴክኒክና ሞያ ሰልጣኞች ሰልጥነው በሚወጡበት ሞያ ላይ በስልጠና በግብዓትና በገንዘብ በኩል ድጋፍ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ለመግባባት እንዲሁም ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጁ ሰልጣኞች በምን ዘርፍና ሞያ መሰልጠን እንዳለባቸው( የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት) ላይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ እንደተናገሩት፤ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጁ ከኢንዱስርሪዎች ጋር የሚያደርገው የጋራ ውይይት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ኢንዱስትሪውም በክህሎት ላይ የትብብር ስልጠና እንዲሰጥ፣ ሰልጣኞች ማሽኖችን በተገቢው እንዲውቁ የራሳቸው ሚና እንዳላቸውም አስረድተዋል፡፡ ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች በጋራ መክረው ያሉትን ክፍተቶች በመለየት የጋራ ምክር አድርገናን ብለዋል፡፡በውይይቱም ቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች የሚያወጧቸው ሰልጣኞች ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉበትን አግባብ ያቀረቡ መሆኑንና ተቋሙም መረዳቱን ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል ስራ ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አማራ አለሙ እንደተናገሩት፤ የቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ የንድፈ ሃሳብ ትምህርትን ከኢንዱስትርዎች የተግባር ትምህርት ጋር በማገናኘት ጥራት ያለው ሰልጣኝ ማውጣት ያስፈልጋል ከ40 በላይ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች በውይይቱ መሳተፋቸውን የገለፁ ሲሆን፤ በዚህ ግንኙነት መሰረት ሰልጥነው የሚወጡ ወጣቶች የክሎት ክፍተት እንደማይኖራቸውም አስረድተዋል፡፡ ሰልጣኞች በቀጣሪ ድርጅቶች ፊት ቀርበው በሞያቸው እንዲያሰለጥኑ እድል ማግኘታቸውና የስራ እድልም እንደሚፈጠርላቸው መደረጉ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡ የተስፋ ኢንተርፕራይዝ ድርጅት ፕሪጀክት ማናጀር ስራ አስኪያጅ አቶ ፍሬው ደሳለኝ እንደገለፁት፤ ኢንዱስትሪዎችና ቴክኒክና ሞያ ኮሌጆችን አንድ ላይ በማድረግ የስልጠና ጥራት እንዲሻሻል ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ውይይቱ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች ከኢንዱስትሪዎች ጋር ተቀራርበው እንዲሰሩ ለማድረግ ያለመ ሲሆን በዚህ መልኩ 2ቱ በስምምነት ሰልጣኖችን እንዲያበቁና የስራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያግዝ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ ድጅቱ በደብረ ብርሃን ከተማ በዚህ ዓመት ከ5 ሺ በላይ ወጣቶችን በተለያዩ ብድርና ስልጠና የሚደግፍ መሆኑንም አስረድተዋል ድርጅቱ በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ በክህሎት ስልጠና ላይ 200ሺ ወጣቶችን እንደ ሀገር ለማሰልጠን ያቀደ ሲሆን ግማሽ ጊዜውን አጠናቋል ብለዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ የደብረ ብርሃን ከተማ ስራ ክህሎት አመራሮች፣ ተመራቂ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
Create your first notice to get started!