Loading...

News and Events

የፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ከደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር የ3ዮሽ ሰምምነት ተፈራረመ።

📅 2025-11-13 11:38:47(23 days ago)

በላይነህ ክንዴ ግሩፕ የፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ከደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ ተመርቀው የወጡ ሰላሳ ሰልጣኞችን ተቀብሎ የተግባር ስልጠና ለመስጠት ስምምነት አድርጓል። ስምምነቱ ፋብሪካው ከ2ቱ ተቋማት የመለመላቸውን ሰልጣኞች ለ4 ወራት አሰልጥኖ ለመቅጠር መሆኑም ተገልጿል። በመርሐ ግብሩ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንዳሉት፤ በከተማው ወደ ማምረት የገቡ ብዙ ፋብሪካዎች ቢኖሩም የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ግን ሞዴል የሚሆን ተግባር እየፈጸመ ነው። በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፋብሪካው ለአካባቢውን ወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል። እንደዚህ አይነት የኢንደስትሪ ትስስሮች ተማሪዎች በተቋማቸው ከሚያገኙት የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በተጨማሪ የተግባር ስልጠና ለማግኘት የሚያስችል ስለመሆኑ አንስተዋል። ይህንን ተግባር ሌሎች በከተማው የሚገኙ ኢንደስትሪዎች በተሞክሮነት በመውሰድ ሰልጣኞችን በመቀበል የተግባር ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል። የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የፌቤላ ኢንዱስትሪያል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እንየው ዋሴ እንደተናገሩት፤ ፋብሪካው የ2ቱን ተቋማት ሰልጣኞች የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በመስጠት በቅጥር ለመውሰድና በሌሎች ስራዎች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ እየሰራ ነው ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ባለሙያው መሰልጠን ያለበት ከዩንቨርስቲና ከቴክኒክ ኮሌጅ ብቻ ሳይሆን ከኢንዱስትሪ ተቋማትም የተግባር ስልጠና መውሰድ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ እንደተናገሩት፤ በኮሌጁ የሰለጠኑ ሰልጣኞች ከሰለጠኑ በኋላ ወደ ኢንዱስትሪው እንዲገቡ ለማድረግ ይህ አይነት ስምምነት ያስፈልጋል። በሰልጣኞቹ የጋራ ስራ መስራት ስላለብንና ብቁ እንዲሆኑ ኢንዱስትሪው የራሱ ድርሻ አለበት ያሉ ሲሆን 2ቱም ባለድርሻ በመሆን እንሰራለን ብለዋል።

Notice image for  የፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ከደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ ጋር የ3ዮሽ ሰምምነት ተፈራረመ።

View All News
29455 views