📅 2026-02-13 01:47:41(Yesterday)
በደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሠጠ። ቀን 5/06/2018ዓ.ም ደብረ ብርሀን በደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ለኮሌጁ አሰልጣኞችና የአስተዳደር ሰራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ። ስልጠናውን ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ባሻዬ በየነ ሲሆኑ ስልጠናው ለተከታታይ ሦስት ቀናቶች የሚወስድ ሲሆን የተቋሙን የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ ፣ አሠራሮችን ለማዘመንና ግንዛቤ ለማዳበር ያግዛል ብለዋል። በኮሌጁ ሰው ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ በአቶ አንተነህ ታሪኩ አማካኝነት የሰራተኞች ትምህርት ማስረጃዎች ማጣራትን በተመለከተ እና በመልካም አስተዳደር በአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የኢንስትራክተሮች ዝዉዉር ምደባ መመሪያን ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው። በተጨማሪም የስራ ስነ- ምግባር ላይ በወ/ሮ ውዴ ሀይሉ በስነ ምግባር ባለሙያ የቀረበ ሲሆን ስልጠናውም በነገው እለት ቀጥሎ ይውላል። # ደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Create your first notice to get started!